You are on page 1of 5

ርስታችንን ብንረሳ የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋን!

………………………
ደጋግመን እንደተናገርነው አማራ የሚባል ብሔር የለም፡፡ አማራ በደጋማው የክልል አካባቢ የሚኖር
ኑሮውን በግብርና ያደረገ የክርስትና ኃይማኖት አማኝ ነው፡፡ ይኼ እኔ ያልኩት ሳይሆን አያሌ የስነ-
ማሕበረሰብና የታሪክ አጥኚዎች የመሰከሩት እውነታ ነው፡፡ ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሽዋ እና ወሎ በሚባሉ ክፍለ
ሀገራት ተከፋፍሎ የሚኖረው አማርኛ ተናጋሪው ሕብረተሰብ ከተለያዩ ህዝቦች ጋር እየተዳቀለ፤ የሌሎችን
መሬት፣ ባህልና ቋንቋ እየወሰደ አሁን ላለንበት ዘመን ደርሷል፡፡

አማራ (ክርስቲያኑ) የመሬት፣ የባህልና የቋንቋ ወረራ ከፈጸመባቸው ህዝቦች መካከል የትግራይ ህዝብ
ቀዳሚው ነው፡፡ አማራ የትግራዋይ የሆነውን ሁሉ ይመኛል፤ ትግራዋይ ለመምሰል የማያደርገው ጥረት
የለም፡፡ ሹሩባው፣ ጌጣጌጡ፣ ህዝባዊ በዓላቱ እንዳለ ከትግራይ የኮረጃቸው ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ ቁጭት
የሚፈጥረው ደግሞ በ19ኛው ክፍለ ዘመን ከውጭ ወራሪዎች ጋር በመመሳጠር ጀግናው ንጉሳችን ሃጼ
ዮሃንስን በማስገደል የፈጸመው የመሬት ወረራ ነው፡፡ በወቅቱ የነበሩ ከተላለዩ ጎሳዎች የተዳቀሉ አማርኛ
የሚናገሩ መሪዎች ከአማራ ጋር በመወገን ስልጣናቸውን ተጠቅመው የትግራይን መሬት ዘርፈውታል፡፡
የሚገርመው ዘመናት ቢያልፉም ባለቤትነታቸውን የሚጠቁም ስማቸውን እንኳ እስካሁን አልቀየሩም፡፡
አብዛኛው ስማቸው አሁንም ትግርኛ ነው፡፡ ዓዲ ኣርቃይ፣ ዓዲ ቀርኒ፣ ዓዲ መደራጉሕ፣ ጽሉም ማይ፣ ማይ
ኣለኮ፣ ኣብዲራፊዕ፣ ኣብርሃ ጅራ፣ ደሚብያ፣ ለማልሞ፣ መተማ፣ ታሕታይ ኣርባጽሖ፣ ኣርማጭሆ
(ሓርማዝጎሀ)፣ ቆቦ እና ሌሎች የትግራይ መሬቶች አሁንም በአማራ ቁጥጥር ስር ናቸው፡፡ እንደነ ዶክተር
ሃብተማርያም አሰፋ ያሉ ምሁራንም ሐቁን በመጽሐፍቶቻቸው በሚገባ ሰነድውታል፡፡

ሆኖም ራሱ አማራ "አልጠግብ ያለው ሲተፋ ያድራል" እንደሚለው አሁንም ወርሮ በያዘው ሊጠግብ
አልቻለም፤ ሌላ ያልወረርኩት መሬት አለኝ እያለ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ በአንድ ሀገር እየኖርን ቁርቁስ ውስጥ
መግባት ስላልፈለግን፤ ሁሉ አገራችን ነው ብለን ስላሰብን እንጂ የተያዘብንን መሬታችንን ረስተን
አይደለንም፤ ፈሪዎች ወይም ሞኝ ሆነንም አይደለም፡፡ አሁን ግን መሬታችንን የምናስመልስበት ጊዜ
ደርሷል፡፡ ኃይል አለን ብለን ጦርነት መክፈት ሳያስፈልገን ከጥንት ዘመን ጀምሮ በውጭ ሀገራት ዜጎችና
በኢትዮጵያውያን የተጻፉትን ሰነዶችን ይዞ ፍርድ ቤት መሄድ ነው፡፡ ሕግ የማይገባው ካለ ወደ ሌላኛው
አማራጭ እንሄዳለን፡፡ አንድ እርግጠኞች ሆነን የምንናገረው ግን መሬታችንን አንረሳም፡፡ ርስታችንን ብነረሳ
የአባቶቻችን አጥንት እሾህ ሆኖ ይውጋን!

You might also like